ከጥሬ ዕቃ ሽያጭ ወደ ወርቅ ክምችት፡ — የአፍሪካ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት አዲስ ምዕራፍ — Continental Drift | Лучшие подкасты на русском языке

ከጥሬ ዕቃ ሽያጭ ወደ ወርቅ ክምችት፡ — የአፍሪካ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት አዲስ ምዕራፍ

13.10.2026 3604

የአፍሪካ ሀገራት የማዕድን ሃብታቸውን በጥሬው ከማስወጣት ባለፈ በአገር ውስጥ እሴት ጨምሮ ማቀነባበር እና የውጭ ምንዛሪ ጥገኝነትን መቀነስ ለኢኮኖሚ ሉዓላዊነታቸው ወሳኝ ነው። ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ቦሌ ለሚ ልዩ ኢኮኖሚ ክልል ያስመረቀችው ብሔራዊ የከበሩ ብረቶች ማጣሪያ ፋብሪካ ተጨማሪ እሴት ለመፍጠር፣ የተሻለ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እና ቀጣናዊ የንግድ ማዕከል ለመሆን ትልቅ ምዕራፍ ነው።

"የአፍሪካ ሀገራት ገንዘባቸውን ለመደገፍ ወርቃቸውን ሸጠው የአሜሪካ ዶላር ከሚገዙ—እንደ ጋና እና ናይጄሪያ ልምድ—የአፍሪካ ማዕከላዊ ባንኮች፣ ማለቴ የአፍሪካ ማዕከላዊ ባንኮች ሁሉ፣ ጋና እያደረገችው እንዳለው ሁሉ የሀገራቸውን ምንዛሪ ጠንካራ መሠረት ለማስያዝ የወርቅ ሀብታቸውን በቀጥታ በሪዘርቭነት መያዝ ይኖርባቸዋል።" ሲሉ አለም አቀፍ የንግድ እና ኢንቨስትመንት አማካሪ ዴኒስ ፐርሲቫል ኩአይኮኢ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የኢትዮጵያን አዲስ የከበሩ ብረቶች ማጣሪያ ፋብሪካ፣ የወርቅ እሴት መጨመር እና የአፍሪካ ማዕከላዊ ባንኮች የወርቅ ሪዘርቭ ፖሊሲ ለአህጉሪቱ ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት ያላቸውን ፋይዳ እንቃኛለን። ለዚህም ዓለም አቀፍ የንግድ እና ኢንቨስትመንት አማካሪ ከሆኑት ከዴኒስ ፐርሲቫል ኩአይኮኢ ጋር ያደረግነውን ቆይታ እናቀርባለን።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን ያዳምጡ።

Другие выпуски

Все выпуски →
Ничего не играет
00:00 / 00:00