የአፍሪካ ዲጂታል ሉዓላዊነት እና ሰዉ ሰራሽ አስተውሎት፡ መሠረተ ልማት፣ የኃይል ፍላጎት እና የፈጠራ አቅም — Continental Drift | Лучшие подкасты на русском языке

የአፍሪካ ዲጂታል ሉዓላዊነት እና ሰዉ ሰራሽ አስተውሎት፡ መሠረተ ልማት፣ የኃይል ፍላጎት እና የፈጠራ አቅም

02.11.2026 3604

የአፍሪካ የዲጂታል ዕድገት እና ሰዉ ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ እውን እንዲሆን መድረኮችንና መሠረተ ልማቶችን ማሟላት ብቻ ሳይሆን፣ የቴክኖሎጂውን የኮምፒዩቲንግ (Compute) እና የኃይል ፍላጎት ማስተናገድ የሚችል አቅም መገንባት ወሳኝ ነው። ባለጸጋ የሆኑ የተማሩ የሰው ኃይሎች ቢኖሩም፣ ለአዳዲስ ፈጠራዎችና ሙከራዎች የሚሆን በራስ መተማመን እና ምቹ ሁኔታን መፍጠር ያስፈልጋል።

«አዎ፣ በእርግጠኝነት። ይህ በአንድ መፍትሄ ብቻ የሚወሰን አይደለም ብዬ አስባለሁ። በሁሉም አቅጣጫዎች መሥራት አለብን። ስለዚህ፣ መድረኮችን መገንባት አለብን። መሠረተ ልማቶችን መገንባት አለብን። መሠረተ ልማቱ የዚህን የቴክኖሎጂ የኮምፒዩቲንግ እና የኃይል ፍላጎቶች ማሟላት የሚችል መሆን አለበት። በእርግጥ የተማረና የሰለጠነ የሰው ኃይል አለን፤ ነገር ግን በራስ መተማመኑ አላቸው ወይ? ስለዚህ ስለ ፈጠራ እና ሙከራ መብት ወደጠቀስኩት ጉዳይ ስንመለስ፣ ባለሙያው የሚፈጥርበት በራስ መተማመን ይፈልጋል። እና አሁንም ያንን አላቸው ብዬ አላስብም።» — ሲሉ የአዲስ ፈውቸርስ ላብ መስራች እና የቬንቸር አጋር መታሰቢያ ዮሴፍ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የአፍሪካን ዲጂታል የወደፊት ዕጣ ፈንታ፣ ሰዉ ሰራሽ አስተውሎት (AI) መሠረተ ልማት እና የኃይል ፍላጎቶች እንዲሁም የአፍሪካ ወጣት ባለሙያዎች በቴክኖሎጂ ልማት ላይ ያላቸውን በራስ መተማመን እና የፈጠራ ምህዳር በሁለት አቅጣጫዎች እንፈትሻለን። ለዚህም የአዲስ ፈውቸርስ ላብ መስራች እና የቬንቸር አጋር ከሆኑት ከመታሰቢያ ዮሴፍ ጋር ቆይታ አድርገናል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

Другие выпуски

Все выпуски →
Ничего не играет
00:00 / 00:00