የኢትዮጵያ ቱሪዝም ዕድገት፡ የመንግስት ቁርጠኝነት እና የኢኮኖሚ ምሰሶዎች
በዛሬው የ ኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የኢትዮጵያን ቱሪዝም ዘርፍ ፈጣን ዕድገት፣ የመንግስትን ቁርጠኝነት እና የኢኮኖሚ ምሰሶነቱን እንዲሁም እንደ እንቁጣጣሽ ያሉ ባህላዊ በዓላትን ወደ ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ምርት መቀየር የሚቻልበትን ሁኔታ እንቃኛለን። ለዚህም የኢትዮጵያ ቱሪዝም እና ሆቴል ገበያ ማህበር ፕሬዚዳንት ጌታሁን አለሙ ጋር አድርገነውን ቆይታ እናቀርባለን።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ።

