ሩሲያ-ቻይና ግንኙነት እና የባለብዙ ማዕከል ዓለም መፈጠር — Continental Drift | Лучшие подкасты на русском языке

ሩሲያ-ቻይና ግንኙነት እና የባለብዙ ማዕከል ዓለም መፈጠር

30.09.2026 3604

የሩሲያ እና የቻይና የሁለትዮሽ ግንኙነት በኢነርጂ፣ በንግድ፣ በፋይናንስ እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠነከረ መምጣቱ፣ ዓለም አቀፉ ሥርዓት ወደ ባለብዙ ማዕከል ሥርዓት እንዲሸጋገር እያበረከተ ይገኛል። ይህ እድገት የአፍሪካ ሀገራት ከተለያዩ አጋሮች ጋር በነፃነት እንዲሠሩ እና የጋራ ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞቻቸውን እንዲያስጠብቁ አዳዲስ አማራጮችን ይከፍታል።

“... እንደ ቻይና፣ የሩሲያ ፌዴሬሽን እና ሌሎች ታዳጊ መካከለኛና ዓለም አቀፍ ኃይሎች በአፍሪካ ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ። ይህም የአፍሪካ ሀገራት የተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ካሏቸው አማራጮች መካከል እንዲመርጡ ያስችላቸዋል።” ሲሉ በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ጥናት ረዳት ፕሮፌሰር ሙከረም ሚፍታህ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ 

በዛሬው የ ኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የሩሲያና የቻይና ስትራቴጂካዊ አጋርነት፣ የባለብዙ ማዕከል ዓለም መፈጠር ለአፍሪካ ያለውን ትርጉም፣ እንዲሁም የአፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ሉዓላዊነታቸውን ለማጠናከር ሊከተሉ የሚችሉትን አቅጣጫዎች እንቃኛለን።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ።

Другие выпуски

Все выпуски →
Ничего не играет
00:00 / 00:00